የነጭ ሽንኩርት 22 የጤና በረከቶች

የነጭ ሽንኩርት 22 የጤና በረከቶች

1. የኮልስትሮል መጠንን ይቀንሳል፡፡
2. ቲቢን ለማከም ይረዳል፡፡
3. የደም ግፊትን ይቀንሳል፡፡
4. ጉንፋንንና ሌሎች መሰል የላይኛው የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ይከላከላል፣ ይፈውሳልም፡፡
5.የባክቴሪያ መራባትንና መዛመትን ይከላከላል፡፡
6. የደም ቅዳ (Artery) ግድግዳዎችን በማደደርና በማጥበብ የሚታወቀውን አቲሮስክሊሮሲስ የተሰኘውን በሽታ ይዋጋል፡፡
7. መግል የቀላቀለ ቁስልን ለማከም ይረዳል፡፡
8. የብልት በሽታ (Trichomoniasis) የሚሰኘውን የአባላዘር በሽታ ለማከም ይረዳል፡፡
9.በህዋሳት ውስጥ የሚካሄደውን ዋንኛውን ኬሚካላዊ ውህደት (Metabolism) ያነቃቃል፡፡
10.ከነቀርሳ (Cancer) ዓይነቶች አንዱ የሆነውን የኮለን ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡
11. የሐሞት ከረጢት ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡ 12. የፊንጢጣ ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡
13. የጡት ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡
14. በወንዶች ላይ የሚከሰተውን የፕሮስቴት ካንሰር መስፋፋትን ይገታል፡፡
15. ለምግብ መፈጨት ሂደት ይረዳል፡፡
16. በልጆች ላይ የሚከሰተውን የማያቋርጥ ሳል ለመከላከል ይረዳል፡፡
17. የእርጅናን ሂደትን በተወሰነ መልኩ ለመግታት ይረዳል፡፡
18. የአንጀት ውስጥ ትላትልና ተህዋስያንን ይገድላል፡፡
19. የምግብ ፍላጎትን ይጨምራል፡፡
20 በአብዛኛው በእድሜ ሳቢያ የሚከሰተውን ካታራክት የተሰኘውን የአይን እይታ ችግርን ለማከም ይረዳል፡፡
21 . የደም መርጋትን ለማሟሟት ይረዳል፡፡
22 . ለስኳር በሽታ ህክምና ይረዳል፡፡
ምንጭ፡ ከሣይንስ ማህደር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *