በአዲስ አበባ 10 ሺህ ሰዎችን የሚያስተናግድ ቤተ-መጽሀፍት ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ በቀን 10 ሺህ ሰዎችን የሚያስተናግድ ቤተ-መጽሀፍት ሊገነባ መሆኑን የከተማይቱ አስተዳደርአስታወቀ።

ቤተ-መጻህፍቱ የሚገነባዉ አራት ኪሎ በሚገኘዉ የተወካዮች ምክር ቤት ህንፃ ፊት ለፊት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት በዛሬዉ ዕለት በፌስቡክ ገጹ ይፋ አድርጓል።

Related image

 
ይህ የህዝብ ቤተ-መጻህፍት ለህጻናትና ለአዋቂዎች የንባብ ቦታ ሆኖ ከማገልገሉ በተጨማሪ የስብሰባ አዳራሾችን እና የትያትር ማዕከላትንም የያዘ ነዉ ተብሏል። ቤተ-መፃህፍቱ 38,687 ስኩየር ኪሎሜትር ስፋት ባለው መሬት ላይ እንደሚገነባ የጠቆመው ፅህፈት ቤቱ ገንብቶ ለማጠናቀቅም ሁለት አመት እንደሚፈጅ ገልጸዋል። 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *