አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ ከሰሩት ድንቅ ሰራዎቹ በጥቂቱ

Image result for gedu andargachew

የዛሬን አያድርገውና የሕወኃት ሰዎችን መናገር ቀርቶ ቀና ብሎ ማየት በመፊራበት የጨለማው ጊዜ አይነኬ የሕወኃት ሰዎችን በመንካት፣ የማይደፈሩ የሚመስሉ የሕወኃት ሰዎችን በመድፈር የደላንታው ወርቅ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቀዳሚ ናቸው፡፡ በእጃቸው መነጸራቸውን ከፍ ዝቅ እያደረጉ ሕወኃቶችን ከፍ ዝቅ አድርገዋቸዋል፡፡

ይህ ተግባራቸው ከራሳቸውም ድርጅት አባላት ሳይቀር ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲነሳባቸው ቢያደርግባቸውም ለመኑበት ሟች የሆኑት ..ሀሞተ ኮስታራው አቶ ገዱን ኋላ ሳያፈገፍጉ ወደ ፊት በመገስገስ ሕወኃት እንድትገረሰስ የአንበሳውን ሚና ተጫውተዋል፡፡በዚህም ተግባራቸው ትውልድ ሲያመሰግናቸው እና ሲዘክራቸው ይኖራል፡፡

Image result for gedu andargachew

ወሎየው አቶ ገዱ የቀድሞው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣ የአ/ብ/ክ/መ የማስታወቂያ ቢሮ ኃላፊ፣በም/ል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአ/ብ/ክ/መ የግብርና ቢሮ ኃላፊ በመጨረሻም ለዶ/ር አምባቸው ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው እስካስረከቡበት ጊዜ ድረስም የአ/ብ/ክ/መ ፕሬዚዳንት በመሆን አገልግለዋል፡፡ አቶ ገዱ የመጀመሪያ ዲግሪ በልማት አስተዳድር እና በ ”Organization Lider ship” 2ኛ ዲግሪ አላቸው፡

አቶ ገዱ ሙስናን ሚጠየፉ፣ ነገሮችን ከግራና ከቀኝ የሚያዩ፣ በጣም የተረጋጉ ፣ሁሉንም ህዝብ በእኩል መነጽር የሚያዩ ትጉህ መሪ ናቸው፡፡አቶ ገዱን በቅርብ ሚያውቋቸው ሰዎች ጥሩ መሪ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ዲፕሎማት መሆናቸውን ይመሰክሩላቸዋል፡፡

አቶ ገዱ ለተገኘው ለውጥ ባበረከቱት ጉልህ ድርሻ ከክልሉ ህዝብ አልፈው በመላው ኢ/ያ የሚወደዱ የሚከበሩ እና የሚታመኑ ናሽናል ፊገር ሆነዋል፡፡ከሀገር ውጭም ባሉ ኢ/ያዊያን ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት እና ተሰሚነት እጅጉን ከፍተኛ ነው፡፡

ለአቶ ገዱ የውጭ ጉዳይ ሚ/ርነት ሲያንሳቸው እንጂ ይበዛባቸዋል የሚል እምነት የለኝም..፡፡ከሁሉም ከሁሉም በላይ ግን የአቶ ገዱ ወደ ፌደራል ደረጃ መጥተው የሚ/ሮች ምክር ቤት አባል መሆን የፌደራል መንግስቱ የሚታዩበትን ክፍተቶች ለመሙላት አቶ ገዱ ጥሩ በር ናቸው፡፡

ምንጭ ሓበሻ ሪፖርት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *