አቶ ለማ መገርሳ ብልፅግናን ደገፉ – ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባትም ተፈታ።

ሰበር መረጃ

SBS ሬድዮ አማርኛው አገልግሎት…

አቶ ለማ መገርሳ ብልፅግናን ደገፉ – ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባትም ተፈታ!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ መካከል ተከስቶ የነበረው አለመግባባት በተከታታይ በአባ ገዳዎችና የአገር ሽማግሌዎች ጋር በተደረገ ውይይት ከመግባባት ላይ መደረሱ ተነግሯል። አቶ ለማ መገርሳ ያለውን ችግር በሂደት ለመፍታትና ከብልፅግና ፓርቲ ጋርም ለመስራት መስማማታቸውን OBN የቴሌቭዥን ጣብያ ማምሻውን ዘግቧል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድና የመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳ መካከል የነበረ አለመግባባት “በበሳል የድርጅታችን ስራ አስፈጻሚ አመራሮችና በቀድሞ የትግል ጓዶች” ተፈቷል ሲል የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አስታውቋል። ዶ/ር አብይ እና አቶ ለማ በጋራ ለመታገል ተስማምተዋል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *