በመንግስት ባለስልጣናት ላይ ያነጣጠረው ግድያ አሁንም ቀጥሏል!

በምዕራብ ኦሮሚያ “በመንግስት ባለስልጣናት” ላይ ያነጣጠረው ግድያ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑ ተነገረ። ትናንት በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ ሁለት የወረዳው ባለስልጣናት ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመተው መገደላቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።

በትናንትናው የጎጆ ከተማ ግድያ ሕይወታቸውን ያጡት የጀልዱ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ረጋኔ ከበደ እና በወረዳው የኦዲፒ ጽ/ቤት የከተማ ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ገረመው መሆናቸውን የወረዳዋ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ባለሞያ አቶ ቢቂላ አበበ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ገልጸዋል።

 

የጀርመን ድምፅ ሬድዮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *