በዛሬው ዕለት በሚካሄደው የኢህአዴግ ምክርቤት ስብሰባ ላይ ህወሓት እንዳይማይሳተፍ ውሳኔ አሳለፈ

የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት ዛሬ  በሚጀመረው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደማይሳተፉ የህወሓት ፅሕፈት ቤት ገለፀ፡፡ ህወሓት በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ በኩል ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢህአዴግ ውህደት በግንባሩ ሥራ አስፈፃሚ ደረጃ ይሁን ምክር ቤት ስብሰባ ሊወሰን የማይችል መሆኑ ጠቅሶ አባላቱ ነገ በሚጀምረው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደማይሳተፉ ዐስታውቋል፡፡

አራቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች እያንዳንዳቸው 45 ተወካዮች የሚያሳትፉበት የኢህአዴግ ምክር ቤት ከነገ ጀምሮ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ግንባሩ በዛሬው ዕለት ገልፅዋል፡፡ «የህወሓት እጣ ፈንታ ሊወሰን የሚችለው በየደጃው ውይይት ከተደረገበት በኋላ በህወሓት ጉባኤ ብቻ በመሆኑ በአሁኑ ሰአትስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የማንችል መኾኑን እናሳውቃለን» ይላል የህወሓት መግለጫ።

ከኢሕአዴግ ምክር ቤት 180 አባላት መካከል 45ቱ የህውሓት አባላት ናቸው፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በግንባሩ ውህደት ዙርያ የቀረበው የጥናት ውጤት በአብላጫ ድምፅ ማፅደቁ ይታወሳል፡፡ ጉዳዩ በግንባሩ ምክር ቤት ደረጃ እንደሚታይም ተገልፆ ነበር፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *