ሰበር መረጃ

ሰበር መረጃ

የጀዋር የጥበቃ ሴክዩሪቲዎች በአስቸኳይ ጥበቃቸውን አቋርጠው እንዲወጡ ታዘዙ።
ከሌሊቱ በ7:30 ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል፡፡ መኪና ልከው ሊወስዷቸው ቢያስቡም አልተሳካም። ኮማንደሩ በስልክ ረጅም ሰዓት ቢያዋራቸውም ጠባቂዎቹ በፍፁም አንወጣም ሌላ ጥበቃ እስኪመደብ ውጡ መባላችን አግባብ አይደለም በማለት ትዕዛዙ ህግንና የአሰራር ደንብን የተከተለ አይደለም በማለት የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ጃዋር አሜሪካ በእሱ ላይ በምታደርገው የወንጀል ምርመራ እንደማያመልጥ የተረዳና ተስፋ የቆረጠ ይመስላል ምክንያቱም ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጋር አላስፈላጊ እንካ ሰላንትያ አይገጥምም ነበር፡፡ የአማሪካን መንግስት በዚህ አመት ብብዙ ሚሊየን ዶላሮች ወደ ጃዋር አካውንት መተላለፉን ምክንያት በማድረግ የገንዘቡ ምንጭ፣ ገንዘቡን የሰጠውን አካል ማንነት እና ገንዘቡ የተሰጠበትን አላማና ለምን እንደሚውል ከዓለም አቀፍ የፀረ ሽብርና የገንዘብ ዝውውር ጋር ግንኙነት ሊኖረው ስለሚችል በሚል መረጃና ጥርጣሬ ምርመራ እያካሄደ ይገኛል፡፡ የአሜሪካን መንግስት በጃዋር ላይ ምርመራ መጀመሩን ያወቀው ጃዋር ከወንጀል ድርጊቱ ምርመራ የሚያመልጥ ስለመሰለው በደመነፍስ ውሳኔ የአሜሪካንን ዜግነት ለመተውና ውሳኔ ላይ ለመድረስ ስለተቸገረ የተለያዩ አካላትን እያማከረ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *