የባርሴሎና አውቶቡስ ሊዮኔል ሜሲን አንፊልድ ላይ ጥሎት ሄዷል

የባርሴሎና አውቶቡስ ሊዮኔል ሜሲን አንፊልድ ላይ ጥሎት ሄዷል፡፡ባርሴሎና በሻምፕዮንስ ሊጉ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ በሊቨርፑል 4ለ0 ከተረታ በኋላ የቡድኑ አውቶብስ ሊዮኔል ሜሲን አንፊልድ ላይ ጥሎት ሄዷል፡፡ሊቨርፑል ባልተጠበቀ መልኩ የ3ለ0 ሽንፈቱን ቀልብሶ ማለፉ አርጀንቲናዊውን አጥቂምሆነ የቡድኑን አባላት አስደንግጧል፡፡

ማንም ለማን በሚቸገርበት አግባብም ባርሴሎና ተሰናብቷል፡፡ 
ከዚህ አስደንጋጭ ሽንፈት በኋላ ሊዮኔል ሜሲ የአበረታች መድኃኒት ምርመራ ከዚያው አንፊልድ ማድረግ ነበረበት፡፡ ነገር ግን የምርመራ ሂደቱ ጊዜ ወሰደበትና ትዕግስት ያልነበረው የቡድኑ አውቶቡስ ጥሎት ወደ አውሮፕላን ማረፊያ አቀና፡፡ 
ነገር ግን በኋላ ሁኔታዎች ተመቻተው ሜሲ የቡድኑን አባላት እንዲቀላቀል ተደረገ፡፡ሰርጂዮ ቡስኬት በውጤቱ ይቅርታ ጠይቋል፡፡ ‹‹ከእኛ የተሻሉ ነበሩ፤ ለዚህ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ሮም ላይ የሆነው ነገር አንፊልድ ላይ ሆኗል፡፡ ብዙ ግብ የማስቆጠር ዕድሎች ነበሩን፤ ግን በዕለቱ አልተሳኩልንም›› ብሏል የባርሴሎናው የመሀል ሞተር፡፡

ምንጭ፡- ሜትሮ
በኪሩቤል ተሾመ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *