በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው፡፡በሠላማዊ ሠልፈኞቹ ‹‹የአማራ መገደልና መፈናቀል ይቁም፤ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት ይጠብቅ›› የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው፡፡ በሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ቤኔሻንጉል ጉሙዝ፣ ራያ ቆቦና ሌሎችም አካባቢዎች ሲከሰቱ የቆዩ የፀጥታ መደፍረሶችና በተለይ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ከሰሞኑ የተቀሰቀሰው ግጭት ያስከተለው ሞትና መፈናቀል ለሰልፎቹ መጠራት ምክንያት እንደሆኑ ታውቋል::

ደብረ ታቦር፣ ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ማርቆስ፣ መርዓዊና ሌሎችም ከተሞች ሰልፎቹ ተጀምረዋል፡፡በየሠላማዊ ሠልፎቹ የሚተላለፉ ዝርዝር መልዕክቶችን ዘጋቢዎቻችን እንዳደረሱን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

ፎቶ፡- ከማኅበራዊ ገፆች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *