የእስልምናው ኘሬዘዳንት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ።

⬆️
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ መሀመድ አሚን ጀማል ያቀረቡት የስራ መልቀቂያ በጉባኤው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ፕሬዚዳንቱ ዛሬ እየተካሄደ ባለው ጉባኤ በጤና ችግር ምክንያት ከዚህ ቀደም ያቀረቡት የስራ መልቀቂያ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ጥያቄ ቢያቀርቡም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።

የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አባላቱ እስካሁን በጥሩ መንገድ ሲመሩት የነበረውን ተቋም ምርጫ እስከሚካሄድ አልያም በቀጣይ ረቡዕ በሚካሄደው ሀገራዊ ጉባኤ መጅሊሱን የተመለከቱ ውሳኔዎች እስከሚታወቁ በሃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

የጤናቸው ጉዳይ አሳሳቢ ቢሆንም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ የተጣለባቸውን ሃይማኖታዊ ሃላፊነት እየተወጡ እንዲቀጥሉም አባላቱ ጥያቄ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ጉባኤው ፕሬዚዳንቱ በሃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ወስኗል። ጉባኤው በመድረኩ በተቋሙ ውስጥ የሚካሄደውን ለውጥ የሚመሩ 10 አባላት ያሉትን ኮሚቴም አዋቅሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *