ቡልቡላ አካባቢ የሄሊኮፕተር አደጋ ደረሰ

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 17/2011ዓ.ም (አብመድ) ንብረትነቱ የ‹ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ› የሆነ ሄሊኮፕተር ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተነስቶ በመብረር ላይ እያላ ቡልቡላ አካባቢ አደጋ ደርሶበታል፡፡ በሄሊኮፕተሩ አምስት መንገዶኞችን እና ሁለት አብራሪዎች እንደነበሩም ታውቋል፡፡

በአደጋው በመንገደኞችም ሆነ በአብራሪዎቹ ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ የኢትዮጵያ ሲቭል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው አስታውቀዋል፡፡የአደጋው ምክንያት እና አጠቃላይ በአደጋው የደረሰው ጉዳት እየተጠራ እንደሚገኝ ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡
ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል ነው፡፡ምንጭ፡- ኤፍ ቢ ሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *