‹‹በሰላምና በእምነት መገንባት ላይ ልናተኩር ይገባል

‹‹በሰላምና በእምነት መገንባት ላይ ልናተኩር ይገባል፡፡›› ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 17/2011ዓ.ም (አብመድ) ‹‹ከበዓለ ስቅለት እና ትንሳኤ ትልቅ ትምህርት ወስደን ሰብዓዊ እና መንፍሳዊ ሞራላችን በሕግ፣ በፍቅርና በሰላም መገንባት ላይ ልናተኩር ይገባል›› ብለዋል ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትሪያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፡፡ 
ብፁዕነታቸው የስቅለት እና የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳቹህ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

‹‹ለኢትዮጵያ ወጥመድ እና ሁሌም እንዳናሸንፍ የሚያደርገን ሕግን መጣሳችን ነው፤ ይህም ኃጢያት ይዞ ይመጣልና ሁላችንም መንፈሳዊ ሞራላችንና ኅሊናችን ልንጠብቀው ይገባል›› ብለዋል ብጹዕነታቸው ባስተላለፉት መልዕክታቸው፡፡ከመንፈሳዊ ሕግ አፈንግጠዉ በስጋዊ ፍልስፍና ብቻ በመገፋት ኢትዮጵያን በማተራመስ ሥራ ላይ ለተጠመዱ ሁሉ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም ብፁዕታቸው ጠይቀዋል፡፡ ‹‹ከበዓለ ስቅለት እና ትንሳኤ ትልቅ ትምህርት ወስደን ሰብዓዊ እና መንፍሳዊ ሞራላችን በሕግ፣ በፍቅር፣ በአንድነት፣ በሰላምና በእምነት መገንባት ላይ ልናተኩር ይገባል›› ነው ያሉት በመልዕክታቸው፡፡ በተለይ እየታዩ ያሉ ጭፍን ጥላቻ፣ ራስ ወዳድነት እና ‹ለኔብቻ ይድላኝ› ባይነት ሊታረሙ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ራሔል ደምሰው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *