ሰዎች የአኗኗር ሁኔታቸው በተለያዩ ምክንያቶች ሲለወጥ ለተለያዩ በሽታዎች እንደሚጋለጡ ተገለጸ

Image result for HEALTH related

በዕድሜ የገፉ ሰዎችን ብቻ ያሰጋሉ የሚባሉት የማይተላለፉ በሽታዎች አሁን የዕድሜ ገደብ ሳያግዳቸው ጉዳት ማድረሳቸው ይነገራል። የልብ፣ የስኳር፣ የደም ዝውውር መስተጓጎል፣ የደም ግፊት፣ እንዲሁም ካንሰር እና የመሳሰሉት በሽታዎች በአብዛኛው የአመጋገብ፣ የእንቅስቃሴ ጉድለት እንዲሁም የስነልቡና አለመረጋጋት ውጤቶች መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ።

የዓለም የጤና ድርጅት እነዚህ ህመሞች የሚያደርሱትን ጉዳት አስመልክቶ ባወጣው መረጃ ሰዎች በየትኛውም የዕድሜ ክልል ቢሆኑ፣ በየትኛውም ሀገር እና አካባቢ ቢኖሩ የአኗኗር ሁኔታቸው በተለያዩ ምክንያቶች ሲለወጥ፤ ለበሽታዎቹ መጋለጣቸው እንደማይቀር ያመለክታል።

Image result for HEALTH related

ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ በቂ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ትንባሆ ማጨስ እንዲሁም የአልክሆል መጠጥን በአደገኛ መልኩ መጠቀም በበሽታዎቹ የመያዝን፤ ምልክቱ ቀድሞ ካለም ደግሞ የማባባስን አጋጣሚ እንደሚያመቻችም ይገልጻል። እንደ የዓለም የጤና ድርጅት ከሆነም በሽታው ያለእቅድ ከሚደረግ የከተሞች መስፋፋት እና ዓለም አቀፋዊነት ካለው የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ጋር ይያያዛል።

ይህም ማለት በእግር ረዥም መንገድ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ይህን ትተው ጉዟቸው በዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ሲወሰን፤ በየጊዜው ትኩስ እና ቤት ውስጥ የተዘጋጁ ምግቦችን ከመመገብ ይልቅ ለረዥም ጊዜ እንዲቆዩ ተደርገው የታሸጉ ምግቦችን መመገብ ሲያዘወትሩ፤ መጠጥ እና ትንባሆ ማጨሱም ሲጠና ሰዎች እነዚህ በሽታዎች ወደራሳቸው እየጋበዙ መሆኑን ልብ እንዲሉት ይመክራል።

ምንጭ ሽዋየ ለገሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *