ሩሲያዊው የኦርቶዶክስ ቄስ በባለቤታቸው “ሀጥያት” ለቅጣት ራቅ ወዳለ ገጠር ተመድበዋል

በሩሲያ ኡራል በምትባል ግዛት የሚኖሩ አንድ የኦርቶዶክስ ቄስ ባለቤታቸው በፆም ወቅት በአካባቢው ቁንጅና ውድድር በመሳተፏ ለቅጣት ሲባል ራቅ ወዳለ ገጠር ተመድበዋል።

ኦክሳና ዞቶፋ የተባለችው ግለሰብ የቁንጅና ሳሎን ያላት ሲሆን ቁንጅና ውድድር ማሸነፏን ተከትሎ ባለቤቱ ያልታወቀው ፒካቡ የተባለ ድረ ገፅ አሸናፊዋ የቄስ ሚስት መሆኗን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ከፍተኛ ትችትን አስተናግዳለች።

የእምነቱ ኃላፊዎች ድርጊቷን ከሰሙ በኋላም ቄሱን ሰርጂ ዞቶፍን በማግኒቶጎርስክ ከተማ ውስጥ ከሚገኘው የእየሱስ እርገት ተብሎ ከሚጠራው ካቴድራል ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ አድርገዋቸዋል።

ከማግኒቶጎርስክ 65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኝ አንዲት መንደር የተመደቡ ሲሆን የህዝብ ቁጥሯም አራት ሺ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

የቤተክርስቲያን አስተዳደርና ጉዳዮችን የሚመለከተው ፍርድ ቤት ኃላፊ የሆኑት ኤጲስ ቆጶስ ፌዮዶር ሳፕሪይክን እንደተናገሩት ” የቄስ ሚስት ራሷን እንዲህ መገላለጧ ከፍተኛ ኃጥያት ነው” ብለዋል

ባለቤታቸው ንስሀ እስከምትገባም ድረስ ወደ ኃላፊነት እንደማይመለሱም ውሳኔ አስተላልፈዋል።

“ቤተሰቡን መቆጣጠር የማይችል ምን አይነት ቄስ ነው? እንዴትስ አድርጎ ነው ጉባኤውን የሚቆጣጠረው” የሚል ጥያቄም አንስተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *